Knygos.lt klubas Knygos.lt nariams
31,70 €
-30%
Įprastai
45,29 €
ቅኔ
ቅኔ
Knygos.lt klubas Knygos.lt nariams
31,70 €
-30%
Įprastai
45,29 €
  • Išsiųsime per 12–18 d.d.
ፍልስፍና ብዙዎች ሱሰኛ የኾኑበት የዓለማችን የዕውቀት የቸዝ ጨዋታ ነው፡፡ ይኽንንም የቸዝ ጥበብ ባለምጡቅ አእምሮ ፈላስፎች ሠርተውታል/…

ቅኔ (el. knyga) (skaityta knyga) | knygos.lt

Atsiliepimai

Aprašymas

ፍልስፍና ብዙዎች ሱሰኛ የኾኑበት የዓለማችን የዕውቀት የቸዝ ጨዋታ ነው፡፡ ይኽንንም የቸዝ ጥበብ ባለምጡቅ አእምሮ ፈላስፎች ሠርተውታል/ፈጥረውታል፡፡ ጨዋታውም በአመክንዮ ተጠየቅ (Logic) እንዲካሔድ ተደርጎ ተቀርጽዋል፡፡ የፍልስፍና ምሁራኑም የቀድሞ ሠሪዎቹን በማድነቅና በማዳነቅ ወይም በመተቸት እየተጫወቱት ኖረዋል/ይኖራሉ፡፡ በጨዋታው ንግሥቷን እውነት ለማግኘትም የማሰብ አቅማቸውን (ዕውቀታቸውን) ኹሉ ተጠቅመው ሲወዳደሩ (ሲከራከሩ) ጊዜያቸውን ይፈጃሉ፡፡ ይኽም ጨዋታ የሚካሔደው በቋንቋ ነው፡፡ ኾኖም ብዙዎቹ ምሁራን በቋንቋ አጠቃቀም ስልት የጨዋታውን ውስብስብነት በመጨመር ያልሠለጠነ ሰው (የፍልስፍና ትምህርት ያልተማረ) የማይደርስበት ክልል ሠርተው አስቀምጠውታል፡፡ እነሱ ግን አጨዋወቱን በመሠልጠንና በማሠልጠን ይለማመዱና የመባልን ይወስዳሉ፡፡ ስለኾነም ማዕረጋቸውንና የሠለጠኑበትን ክልል ለማስጠበቅ የጨዋታውን ሜዳ በሥነ አመክንዮ አጥር ስላጠሩት ማን ደፍሮ ይግባበት?...

... በቸዝ ጨዋታ ሥልጠና የተጠመዱ ብዙዎቹ አካዳሚዊ የፍልስፍና ምሁራንም ሥልጠናውን የወሰዱት ፍልስፍና በተሠራበት በምክንያት ዘይቤ ብቻ ስለኾነ ፍልስፍና ቅኔነት የሌለው ጥበብ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ምሁራኑን የሥልጠና ተፅእኖ ይዟቸው እንጂ የፍልስፍና ጥበብ የሚገኘው በቅኔነት ተቃኝቶ መኾኑ እርግጥ ነው፡፡ ችግሩ ግን በቸዝ ጨዋታ የማመክነይ (የምክንያታዊነት) ሕግ ብቻ መሸበብና ቅኔነትን ከዐለማወቅ የሚመነጭ መኾኑ ላስተዋለው ሰው ግልጽ ይኾንለታል። ፍልስፍና በተፈጥሮው ቅኔነት ባይኖረው ኖሮም ተራ ጥበብ ኾኖ ይቀር ነበር፡፡ ማመክነይ ብቻ እንጂ መደነቅ የፍልስፍና መሠረት መኾን አይችልም ነበር፡፡ ይኽንን ለመረዳት ምናልባት የፍልስፍናን መሠረታዊ ዕሳቤዎች ከቅኔነት ተፈጥሮ ጋር በማነጻጸር ማየት ይጠይቅ ይኾናል፡፡

ለምሳሌ የፍልስፍና ጥበብ (፩) በመደነቅ (Wondering) ላይ መመሥረቱ፣ (፪) ሥርወቃላዊ ትርጓሜው ጥበብን ማፍቀር (Love of Wisdom) መኾኑ፣ (፫) የመጨረሻ ጎሉ/ዓላማው እውነትን (ከቅኔ አንጻር ወርቅን/ምሥጢርን) ፈልጎ ማግኘት (pursuit of Truth) መኾኑ፣ (፬) የህላዌ እንቆቅልሽን (ምሥጢረ ህላዌን- Ontology/ metaphysics) መሠረት አድርጎ የሚጠና መኾኑ፣ (፭) የዐዲስ ሐሳብ/ ዕይታ ናፋቂነቱ (ወዳጅነቱ) (New View/Perspective)... በቅኔነት መሠረት ላይ የሚገኝ መኾኑን ይመሰክራል፡፡ ምናልባት እነዚህ ነጥቦች ቅኔነትን አይገልጹም የሚል ካለ የቅኔነትን ምሥጢር ወደ ውስጥ ሲገባ ይረዳዋል፡፡ በዐጭሩ ቅኔነት በግልጽ ነገር ላይ ተመሥርቶ አንድ የተደበቀ ምሥጢር ወይም ያልታወቀ ሥውር ነገር ተመርምሮ/ ተመሥጥሮ የሚወጣበት ወይም ጎልቶ የሚገለጽበት ጥበብ ነው፡፡

ቅኔ የምሥጢር ቋት እና የሰምና ወርቅ ግዛት ነው፡፡ የእሱም ንጉሡ አእምሮ ሲኾን በ

Knygos.lt klubas
Knygos.lt nariams
31,70 €
-30%
Įprastai
45,29 €
Kaina registruotiems pirkėjams
Prisijunkite ir už šią prekę
gausite 0,45 Knygų Eurų!?
Išsiųsime per 12–18 d.d.
Įsigykite dovanų kuponą
Daugiau

ፍልስፍና ብዙዎች ሱሰኛ የኾኑበት የዓለማችን የዕውቀት የቸዝ ጨዋታ ነው፡፡ ይኽንንም የቸዝ ጥበብ ባለምጡቅ አእምሮ ፈላስፎች ሠርተውታል/ፈጥረውታል፡፡ ጨዋታውም በአመክንዮ ተጠየቅ (Logic) እንዲካሔድ ተደርጎ ተቀርጽዋል፡፡ የፍልስፍና ምሁራኑም የቀድሞ ሠሪዎቹን በማድነቅና በማዳነቅ ወይም በመተቸት እየተጫወቱት ኖረዋል/ይኖራሉ፡፡ በጨዋታው ንግሥቷን እውነት ለማግኘትም የማሰብ አቅማቸውን (ዕውቀታቸውን) ኹሉ ተጠቅመው ሲወዳደሩ (ሲከራከሩ) ጊዜያቸውን ይፈጃሉ፡፡ ይኽም ጨዋታ የሚካሔደው በቋንቋ ነው፡፡ ኾኖም ብዙዎቹ ምሁራን በቋንቋ አጠቃቀም ስልት የጨዋታውን ውስብስብነት በመጨመር ያልሠለጠነ ሰው (የፍልስፍና ትምህርት ያልተማረ) የማይደርስበት ክልል ሠርተው አስቀምጠውታል፡፡ እነሱ ግን አጨዋወቱን በመሠልጠንና በማሠልጠን ይለማመዱና የመባልን ይወስዳሉ፡፡ ስለኾነም ማዕረጋቸውንና የሠለጠኑበትን ክልል ለማስጠበቅ የጨዋታውን ሜዳ በሥነ አመክንዮ አጥር ስላጠሩት ማን ደፍሮ ይግባበት?...

... በቸዝ ጨዋታ ሥልጠና የተጠመዱ ብዙዎቹ አካዳሚዊ የፍልስፍና ምሁራንም ሥልጠናውን የወሰዱት ፍልስፍና በተሠራበት በምክንያት ዘይቤ ብቻ ስለኾነ ፍልስፍና ቅኔነት የሌለው ጥበብ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ምሁራኑን የሥልጠና ተፅእኖ ይዟቸው እንጂ የፍልስፍና ጥበብ የሚገኘው በቅኔነት ተቃኝቶ መኾኑ እርግጥ ነው፡፡ ችግሩ ግን በቸዝ ጨዋታ የማመክነይ (የምክንያታዊነት) ሕግ ብቻ መሸበብና ቅኔነትን ከዐለማወቅ የሚመነጭ መኾኑ ላስተዋለው ሰው ግልጽ ይኾንለታል። ፍልስፍና በተፈጥሮው ቅኔነት ባይኖረው ኖሮም ተራ ጥበብ ኾኖ ይቀር ነበር፡፡ ማመክነይ ብቻ እንጂ መደነቅ የፍልስፍና መሠረት መኾን አይችልም ነበር፡፡ ይኽንን ለመረዳት ምናልባት የፍልስፍናን መሠረታዊ ዕሳቤዎች ከቅኔነት ተፈጥሮ ጋር በማነጻጸር ማየት ይጠይቅ ይኾናል፡፡

ለምሳሌ የፍልስፍና ጥበብ (፩) በመደነቅ (Wondering) ላይ መመሥረቱ፣ (፪) ሥርወቃላዊ ትርጓሜው ጥበብን ማፍቀር (Love of Wisdom) መኾኑ፣ (፫) የመጨረሻ ጎሉ/ዓላማው እውነትን (ከቅኔ አንጻር ወርቅን/ምሥጢርን) ፈልጎ ማግኘት (pursuit of Truth) መኾኑ፣ (፬) የህላዌ እንቆቅልሽን (ምሥጢረ ህላዌን- Ontology/ metaphysics) መሠረት አድርጎ የሚጠና መኾኑ፣ (፭) የዐዲስ ሐሳብ/ ዕይታ ናፋቂነቱ (ወዳጅነቱ) (New View/Perspective)... በቅኔነት መሠረት ላይ የሚገኝ መኾኑን ይመሰክራል፡፡ ምናልባት እነዚህ ነጥቦች ቅኔነትን አይገልጹም የሚል ካለ የቅኔነትን ምሥጢር ወደ ውስጥ ሲገባ ይረዳዋል፡፡ በዐጭሩ ቅኔነት በግልጽ ነገር ላይ ተመሥርቶ አንድ የተደበቀ ምሥጢር ወይም ያልታወቀ ሥውር ነገር ተመርምሮ/ ተመሥጥሮ የሚወጣበት ወይም ጎልቶ የሚገለጽበት ጥበብ ነው፡፡

ቅኔ የምሥጢር ቋት እና የሰምና ወርቅ ግዛት ነው፡፡ የእሱም ንጉሡ አእምሮ ሲኾን በ

Atsiliepimai

  • Atsiliepimų nėra
0 pirkėjai įvertino šią prekę.
5
0%
4
0%
3
0%
2
0%
1
0%
(rodomas nebus)